Get In Touch
Bole, Africa Avenue Addis Ababa Ethiopia
Email info@orointbank.com
Ph: + 251 115 572 002
P.O.Box: 27530/1000 Addis Ababa,Ethiopia
Fax: + 251 115 572 002
SWIFT CODE: ORIRETAA

የገበያ እና የተደራሽነት ንቅናቄ – በሰንዳፋ በኬ

ኦሮሚያ ባንክ በሰንዳፋ በኬ ከተማ ባካሄደው የገበያ እና የተደራሽነት ንቅናቄ 300 ለሚሆኑ አርሶ አደሮች ለክረምት ስራ የሚያግዝ ጫማዎችን አበረከተ።

በዚህ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኦሮሚያ ባንክ እና የሰንዳፋ በኬ ከተማ የግብርና ቢሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ከሰንዳፋ በኬ እና አከባቢው የተወጣጡ አርሶ አደሮች ተገኝተዋል።

አርሶ አደሮቻችንን እና አርብቶ አደሩን በልዩነት ለመደገፍ እና የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን ታስቦ የተቀረፀው ሱቢ ልዩ የአርሶ አደሮች የቁጠባ ሂሳብን ጨምሮ በባንካችን ምርት እና አገልግሎቶች ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ለተሳታፊዎች ተሰጥቷል።

ባንካችን ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት ከመሰጠት ባሻገር አርሶ አደሩን ያማከለ በርካታ የፋይናንስ አማራጮች በማቅረብ ለሀገራችን የግብርና ዘርፍ እድገት በጎ አስተዋዕፆ እያበረከተ ይገኛል።

ኦሮሚያ ባንክ በተመሳሳይ መልኩ በቱሉ ቦሎ፣ በሆለታ እና ጅማ ከተማዎች አርሶ አደሩን ማዕከል ያደረገ ንቅናቄ ማዘጋጀቱ የቅርብ ቀን ትውስታ ነው።