ኦሮሚያ ባንክ በጅማ ከተማ ባካሄደው የገበያ እና የተደራሽነት ንቅናቄ 300 ለሚሆኑ አርሷደሮች ለክረምት ስራ የሚያግዝ ጫማዎችን አበረከተ።
በዚህ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኦሮሚያ ባንክ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የጅማ ከተማ እና አከባቢው አርሶ አደሮች ተገኝተዋል።
በስነ ሥነ-ሥርዓቱ ላይም አርሷአደሩን በልዩነት የሚጠቅም ሱቢ ልዩ የአርሷ አደሮች የቁጠባ ሂሳብን ጨምሮ በባንካችን ምርት እና አገልግሎቶች ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ለተሳታፊዎች ተሰጥቷል።
ባንክችን አርሷደሩን ያማከለ በርካታ የፋይናንስ አማራጮች በማቅረብ ለሀገራችን የግብርና እድገት በጎ አስተዋዕፆ እያበረከተ እንደሚገኝ ይታወቃል።
ኦሮሚያ ባንክ በተመሳሳይ መልኩ በቱሉ ቦሎ እና በሆለታ ከተማ አርሶ አደሩን ማዕከል ያደረገ ንቅናቄ ማዘጋጀቱ የሚታወስ ነው።