Get In Touch
Bole, Africa Avenue Addis Ababa Ethiopia
Email info@orointbank.com
Ph: + 251 115 572 002
P.O.Box: 27530/1000 Addis Ababa,Ethiopia
Fax: + 251 115 572 002
SWIFT CODE: ORIRETAA

ኦሮሚያ ባንክ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት እጅግ ስኬታማ ዘመን ማሳለፉ ተገለጸ፡፡

ኦሮሚያ ባንክ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት እጅግ ስኬታማ ዘመን ማሳለፉ ተገለጸ፡፡

የኦሮሚያ ባንክ አ.ማ 14ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በሚሊኒየም አዳራሽ አካሄዷል፡፡

በጉባኤዉ ላይ ለባለ አክሲዮኖች ከቀረበዉ ሪፖርት ለመረዳት እንደተቻለዉ ባንኩ በተጠናቀቀዉ የበጀት ዓመት በቁልፍ የአፈፃፀም መለኪያዎች የላቀ አፈፃፀም ማስመዝገቡ ተመልክቷል፡፡

ምንም እንኳ የዉስጥ እና የዉጭ ተግዳሮቶች ቢኖሩም  ባንካችን-ኦሮሚያ ባንክ  ወርቃማ የስኬት ዘመን አሳልፏል፡፡ ባለፈዉ የበጀት ዓመት እስከ ሰኔ 30 ድረስ 103 ተጨማሪ ቅርንጫፎች የተከፈቱ ሲሆኑ በአጠቃላይ  የቅርንጫፎቹን ብዛት 503 አደርሷል። የአስቀማጭ ደንበኞች ብዛት በ34 በመቶ አድጓል በዚህም ባንኩ 4.2 ሚሊየን ደንበኞች ማፍራት ችሏል፡፡ የተቀማጭ ሀብት አሰባሰብ አፈፃፀሙ የ24 በመቶ እድገት ያሳየ ሲሆን እ.ኤ.አ. በሰኔ 30 ቀን 2023 ብር 54.3 ቢሊዮን ደርሷል።

በዓለም አቀፍ የባንክ ስራዎች 371 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት የተቻለ ሲሆን አፈፃፀሙ የ32.8 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ ይህም ከእንዱስትሪዉ የተሻለ እድገት ሆኖ ተመዝግቧል፡
በሰኔ 30 ቀን 2023 የባንኩ አጠቃላይ ሀብት የ27 በመቶ እድገት በማሳየት ብር 66 ቢሊዮን ደርሷል። ከወለድ ነፃ የባንክ ፋይናንስን ጨምሮ በብድር፣  በቅድመ ክፍያ እና ፋይናንስ አቅርቦት ላይ 25 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ ከተቀማጭ ዕድገት ጋር በማጣጣም ብር 42.69 ቢሊየን ያገኘ ሲሆን ከወለድ ነፃ የሆነ የብድር መጠን አንፃር በጣም ጤናማ ነዉ፡፡ በ14-አመት ታርኩ ይህ የሀብት ጥራት ቁልፍ አፈፃፀም አመላካች በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ የባንኩን ጤናማነት የሚያሳይ ነው።

የኦሮሚያ ባንክ በዓመቱ ያስመዘገበው የፋይናንሺያል ትርፋማነት በጣም አበረታች እድገት አሳይቷል። በዚህም መሰረት አጠቃላይ ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት በ43 በመቶ  አድጓል፡፡አጠቃላይ የገቢ እድገቱ ከጠቅላላ የወጪ ዕድገት በተሻለ ሁኔታ እየተጓዘ እና ጤናማ የገቢ-ወጪ መዋቅር ያሳያል፡፡ በዚህም ምክንያት ያልተጣራ ትርፍ 2 ቢሊዮን የሚጠጋ  አትርፏል፡፡ ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 63% እድገት አሳይቷል፡፡
በመጨረሻም ጠቅላላ ጉባኤዉ ለቀጣይ ሶስት ዓመታት ባንኩን የሚመሩ የቦርድ አባላት ምርጫ በማድረግ በሰላም ተጠናቋል፡፡