Get In Touch
Bole, Africa Avenue Addis Ababa Ethiopia
Email info@orointbank.com
Ph: + 251 115 572 002
P.O.Box: 27530/1000 Addis Ababa,Ethiopia
Fax: + 251 115 572 002
SWIFT CODE: ORIRETAA

ኦሮሚያ ባንክ ከኢትዮጵያ የዕድሮች ጥምረት ም/ቤት ጋር በአጋርነት ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የባንካችን አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ዘርፍ ቺፍ ኦፊሰር ኦቦ ጆቴ ቀናቴ እና የኢትዮጵያ ዕድሮች ጥምረት ም/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ታምራት ገ/ማርያም ናቸዉ፡፡

የስምምነቱ ዋና አላማም ሁለቱ አጋር ተቋማት በስልጠና እና አቅም ግንባታ፣ በማህበራዊ ሃላፊነት እንዲሁም በሌሎች የምጣኔ ሀብት ችግር ፈቺ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

በመድረኩ ላይ ከተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች የተወጣጡ የእድር ማህበራት ዓመራሮች የተገኙ ሲሆን፣ ባንኩ ለእድሮች እና ማህበራት ስላዘጋጀዉ አማራጭ የባንክ አግልግሎት ላይ ለተሳታፊዎች ገለፃ ተደርጓል።

ኦሮሚያ ባንክ እድሮችን ጨምሮ የተለያዩ ማህበራዊ አደረጃጀቶች እና አባላቶቻቸዉን በልዩነት ተጠቃሚ የሚያደርግ አማራጭ የባንክ አገልግሎት በማቅረብ ሁለተንተነዊ ተጠቃሚነታቸዉን ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል፡፡