ኦሮሚያ ባንክ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር የሀገራችንን ስም እና ሰንደቅ አላማ በአለም አደባባይ ከፍ አድርገዉ የሚያሳዩ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት የስፓርቱን ዘርፍ እየደገፈ ይገኛል፡፡ በዉድድሩ ላይ ባንካችን ከእስፓርት ቤተሰቡ እና ከአዋሳ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የመገናኘት እድል በማግኘት ምርት እና አገልግሎቶቹን አስተዋዉቋል፡፡
በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የተካሄደዉ 40ኛዉ የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ዉድድር በሁለቱም ፆታ ኦሮሚያ ፓሊስ ስፓርት ክለብ የበላይነቱን የወሰደ ሲሆን በወንዶች ጎሳ አምሳሉ እና በሴቶች ኩረኒ ጀሊላ አሸናፊ ሆነዋል፡፡
በዉድድሩ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ክብርት ረዳት ኮሚሺነር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ የኦሮሚያ ባንክ እና የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ባንካችን በቀጣይም መሰል ዉድድሮችን በመደገፍ ለሀገራችን መልካም ስም እና ዝና ላይ በበጎ መልኩ ተፅዕኖ በሚፈጥሩ ስራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡